ኢትዮጵያ

በመጪዎቹ በዓላት የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ ካጋጠመ በፍጥነት የሚጠግን ግብረ-ኃይል ተዘጋጅቷል:- የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት

በመጪዎቹ በዓላት የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ ካጋጠመ በፍጥነት የሚጠግን ግብረ-ኃይል ተዘጋጅቷል:- የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ(ኤ ኤም ኤን) ሚያዚያ 6/2015 ዓም

በመጪዎቹ በዓላት የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ ችግር ካጋጠመ በፍጥነት የሚጠግን ግብረ-ኃይል መዘጋጀቱን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ገለጸ።

የፋሲካና የዒድ አልፈጥር በዓላት በሚከበሩባቸው ቀናት ሊያጋጥም የሚችለውን የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ ችግር ለመፍታት በቂ ዝግጅት ስለመደረጉ አገልግሎቱ አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ መላኩ ታዬ ተቋሙ ያደረገውን ቅድመ-ዝግጅት በማስመልከት ከኢዜአ ጋር ቆይታ አድርገዋል።

በዚህም ለበዓላቱ አከባበር የኃይል መቆራረጥ ችግር እንዳይከሰት አስቀድሞ የማስተካከያ ሥራዎች መከናወናቸውን ገልጸዋል።

የኃይል መቆራረጥ ችግር ቢያጋጥም እንኳን በአስቸኳይ ጥገና የሚያደርግ የባለሙያዎች ግብረ-ኃይል ዝግጁ መሆኑን አረጋግጠዋል።

በበዓላቱ ዋዜማና በእለቱ የደንበኞች የኃይል አጠቃቀም ከፍተኛ በመሆኑ የኃይል መቆራረጥ ችግርን መቀነስ የሚያስችሉ ስራዎች መሰራታቸውን ነው አቶ መላኩ የጠቆሙት።

በዚህም ከዋዜማው ጀምሮ ከኤክስፖርትና ከሲሚንቶ አምራች ፋብሪካዎች ውጭ ያሉ ኢንዱስትሪዎች ከኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ማስተላለፊያና ማከፋፈያ ሥርዓት (ግሪድ) የሚጠቀሙትን ኃይል ያቋርጣሉ ብለዋል።

ህብረተሰቡ የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ በማይበዛበት ጊዜ ማለትም ከምሽቱ 3 ሰዓት እስከ ንጋቱ 11 ሰዓት ባሉት ጊዜያት እንዲጠቀምም አቶ መላኩ መክረዋል።

ለኃይል ፍጆታ ካርድ የሚሞሉ ደንበኞች በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የተለያዩ ማዕከላት መሙላት ይችላሉ ብለዋል።

ተመሳሳይ ልጥፎች

የገጠር መንገድ ተደራሽነትን በማስፋት የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የሚያስችል ፕሮጀክት ይፋ ሆነ

admin

በመጪዎቹ ሁለት ዓመታት በተልዕኮና ትኩረት መስካቸው የተለዩ 9 ዩኒቨርስቲዎችን ወደ ራስ ገዝ ደረጃ ለማሻገር እየተሰራ ነው: – የትምህርት ሚኒስቴር

admin

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በቢክ ኢትዮጵያ የተዘጋጀውን ውድድር አሸነፈ።

admin

አስተያየት ይስጡ