
በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የተጀመሩ የሌማት ትሩፋቶችን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ መጎብኘታቸውን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡
አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ(ኤ ኤም ኤን) ሚያዚያ 6/2015 ዓም
በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የተጀመሩ የሌማት ትሩፋቶችን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ መጎብኘታቸውን ከንቲባ አዳነች አቤቤ አስታውቀዋል፡፡
በሌማት ትሩፋት የኑሮ ጫናን ለማቅለል የተጀመሩ የዶሮ እርባታ ሼዶች እና የወተት ላም “የለሚ ክላስተር” 15,000 ዶሮዎችን ለገበያ በማቅረብ የበዓል ገበያን በማረጋጋት ረገድ ጉልህ ሚና እያበረከተ መሆኑን ከንቲባ አዳነች በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልእክት ገልጸዋል፡፡