አዲስ አበባ

አዲስ አበባ አካባቢያዊነትን፣ ሀገራዊነትን እና ዓለም አቀፋዊነትን ያጣጣመች ከተማ እንድትሆን መስራት ያስፈልጋል-ዲያቆን ዳንኤል ክብረት

አዲስ አበባ አካባቢያዊነትን፣ ሀገራዊነትን እና ዓለም አቀፋዊነትን ያጣጣመች ከተማ እንድትሆን መስራት ያስፈልጋል-ዲያቆን ዳንኤል ክብረት

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ(ኤ ኤም ኤን) ግንቦት 01/2015 ዓ.ም
“አዲስ አበባን በአዲስ የዲፕሎማሲ ከፍታ” በሚል መሪ ሃሳብ ከተማዋን ተመራጭ የዲፕሎማሲ ማዕከል አድርጎ ማስቀጠል በሚቻልበት ሁኔታ ላይ የምክክር መድረክ እየተካሄደ ነው።

በምክክር መድረኩ ላይ የተለያዩ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ የታሪክ ምሁራን፣ የኪነጥበብ ባለሙያዎች፣ የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች፣ዲፕሎማቶች እና ሌሎች እንግዶች ተገኝተዋል።

በመድረኩ መክፈቻ ላይ ንግግር ያደረጉት የጠቅላይ ሚኒስትሩ ማህበራዊ ጉዳይ አማካሪ ሚኒስትር ዲያቆን ዳንኤል ክብረት፤ አዲስ አበባ አካባቢያዊነትን፣ ሀገራዊነትን እና ዓለም አቀፋዊትን ያጣጣመች ከተማ እንድትሆን መስራት ያስፈልጋል ብለዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በመወከል በመድረኩ ላይ ንግግር ያደረጉት አምባሳደር እሸቴ ጥላሁን አዲስ አበባ ተመራጭ የዲፕሎማሲ ከተማ ሆና እንድትቀጥል ከሌሎች ከተሞች ልምድ መውሰድ ይኖርባታል ብለዋል።

የምክክር መድረኩ በኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት የተዘጋጀ ሲሆን በተለያዩ አካላት ከተማዋን የተመለከቱ መነሻ ሀሳቦች ቀርበዋል።

በአሰግድ ኪ/ማርያም

ተመሳሳይ ልጥፎች

በቴክኔክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጆቻችን በተለያዩ የሙያ መስኮች ያሰለጠናችውን 6244 ተመራቂዎች ዛሬ አስመርቀናል” ፡- ከንቲባ አዳነች አቤቤ

admin

ምግባረ ሰናይ የአረጋውያን፣የአካል ጉዳተኞች እና የህፃናት መርጃ ማእከል ወደ መቄዶኒያ አረጋውያን ማቆያ ማእከልነት ተሸጋገረ።

admin

“በቴክኔክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጆቻችን በተለያዩ የሙያ መስኮች ያሰለጠናችውን 6244 ተመራቂዎች ዛሬ አስመርቀናል” ፡- ከንቲባ አዳነች አቤቤ

admin

አስተያየት ይስጡ