
በኦሮሚያ ክልል ባለፉት ወራት የበጋ የመስኖ ስንዴ ልማት እስካሁን ከ26 ሚሊዮን ኩንታል በላይ የስንዴ ምርት መሰብሰብ መቻሉን የኦሮሚያ ኮሙኑኬሽን ቢሮ አስታወቀ
አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ(ኤ ኤም ኤን) ግንቦት 01/2015 ዓ.ም
በኦሮሚያ ክልል ባለፉት ወራት የበጋ የመስኖ ስንዴ ልማት እስካሁን ከ26 ሚሊዮን ኩንታል በላይ የስንዴ ምርት መስብሰብ መቻሉን የኦሮሚያ ኮሙኑኬሽን ቢሮ አስታወቀ፡፡
የኦሮሚያ ኮሙኒኬሽን ቢሮ በክልሉ የተከናወኑ የልማት ስራዎችን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል፡፡
የቢሮዉ ሃላፊ አቶ ሃይሉ አዱኛ በክልሉ በተያዘዉ በጀት አመት በእስካሁን የበጋ ወራት 1.1 ሚሊየን ሄክታር በላይ መሬት በመስኖ መሸፈኑን ጠቁመዋል፡፡
በዚህም የመስኖ ሽፋን ከ26 ሚሊዮን ኩንታል በላይ የስንዴ ምርት መስብሰብ መቻሉን አስታውቀዋል፡፡
ምርትና ምርታማነትን ለማሳድግ ዘመናዊና የተሻሻሉ አሰራሮችን ለማስተዋወቅም ለአርሶ አደሮች ትራክተር እና ማዳበሪያን ጨምሮ የተለያዩ ግብዓቶች መቅረባቸውንም ሃላፊዉ ተናግረዋል፡፡
በዘንድሮዉ አመት ለ1.6 ሚሊየን ለሚሆኑ ስራ ፈላጊዎች በቋሚነት እንዲሁም ከ455 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች ደግሞ በጊዜያዊነት የስራ እድል መፈጠሩንም ሃላፊዉ ገልጸዋል፡፡
በክልሉ የህብረተሰቡን ችግር የሚቀርፉ ከ94 ቢሊዮን በላይ በሆነ ወጭ ከ16 ሺህ በላይ የተለያዩ ፕሮጀክችን እየተገነቡ እንደሚገኝም ሃላፊው ጠቁመዋል፡፡
ለ5ኛዉ ዙር የአርንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ከ4.6 ሚሊየን በላይ ችግኞች መዘጋጀታቸውንም ሃላፊው አቶ ሃይሉ በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል፡፡
በቴዎድሮስ ይሳ