
“ኢትዮጵያ ማምረት ትችላለች“:-የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት
አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ (ኤ ኤምኤን) ግንቦት 1/2015 ዓም
ኅብረትን፤ ልማትን፤ አንድነትን ገንዘብ ካደረግን ኢትዮጵያ ማምረት ትችላለች ሲል የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት አስታውቋል ፡፡
በቂ መሬት፤ በቂ ውኃ፣ ሊያመርት የሚችል በቂ ወጣት፤ ምርትን መደገፍ የሚችል ኢነርጂ፤ በንጽጽር ሻል ያለ የፋይናንስ አቅርቦት፤ አስቻይ የሆነ የማምረቻ ዐውድ ኢትዮጵያ ውስጥ እንዳለም አመልክቷል።
በማዕድን ዘርፍ የተጀመሩ ሥራዎች ለኢንዱስትሪው በከፍተኛ ደረጃ ግብዐት መሆን ይችላሉ ያለው ጽ/ቤቱ በግብርና ዘርፍ የተጀመሩ ሥራዎች በከፍተኛ ደረጃ ለኢንዱስትሪው ግብዐት መሆን ይችላሉ፤ ከፍተኛ የማደግ ፍላጎትም አለን ብሏል።
ስለዚህም የልማትን ምርት ማረጋገጥ እንችላለን ሲልም አመልክቷል