አትሌቲክስ

ለ19ኛው የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በዝግጅት ላይ የሚገኙ አትሌቶች በወቅታዊ ብቃታቸው የተሻሉ እንደሆኑ ተገለፀ

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ( ኤ ኤም ኤን) ሀምሌ 23 ቀን 2015 ዓ.ም

ለ19ኛው የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በዝግጅት ላይ የሚገኙ የኢትዮጵያ አትሌቶች በወቅታዊ ብቃታቸው የተሻሉ እንደሆኑ ተገለፀ።

የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር መስፍን ቸርነት በዛሬው እለት ለ19ኛው የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በዝግጅት ላይ የሚገኙ የወንዶች እና የሴቶች የማራቶን ቡድንን በልምምድ ስፍራ በመገኘት ጎብኝተዋል፡፡

ተመርጠው በቡድኑ ውስጥ የተካተቱት የቡድኑ አባላት ላለፉት ሁለት ወራት ያክል በጋራ ዝግጅት ላይ እንዳሉም ተገልጿል፡፡

ሚኒስትር ዴኤታው እንደገለጹት በዚህ ዝግጅት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ጥራትና ብቃት ያላቸው አትሌቶች እንዳሉት መመልከታቸውንና በወቅታዊ ብቃታቸው የተሻሉ እንደሆኑም ተናግረዋል፡፡

ቡድኑ ጥሩ ሚኒማ ያሟሉና በ18ኛው የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና አሜሪካ ኦሪገን ላይ አሸንፈው የነበሩ በወንዶች ታምራት እና በሴቶች ጎይተቶም ይገኙበታል፡፡

አሰልጣኞችም ደረጃውን የመጠነና ከጊዜውም ጋር የሚሄድ ስልጠና እየሰጡ እንደሆነ ተገንዝበናል ብለዋል።

ከዚህም ባሻገር አትሌቶቹ በአለም ላይ ካስመዘገቡት ሚኒማዎች ባሻገር በጣም ተቀራራቢ ብቃት ላይ ናቸው ሲሉ አምባሳደሩ ተናግረዋል፡፡

በ18ኛው የአለም የአትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ ኢትዮጵያ 4 ወርቅ፣ 4 ብር እና 2 ነሀስ በመያዝ በአለም ላይ ሁለተኛ ሆና ማጠናቀቋ ይታወሳል።

አሁንም ያንን ውጤት መድገም የሚያስችል ጥሩ ዝግጅት እየተደረገ እንዳለ በተለይ የማራቶን ቡድን ጠንካራ እንደሆነ ተገንዝቢያለሁ ሲሉ ገልጸዋል፡፡

በጉብኝቱ ወቅት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ረዳት ኮሚሽነር አትሌት ደራርቱ ቱሉ፣ ምክትል ተቀዳሚ ፕሬዚዳንት አትሌት ገዛኸኝ አበራ፣ የፌዴሬሽኑ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት እና የብሔራዊ ቡድኑ የማራቶን አትሌቲክስ አሰልጣኞች መገኘታቸውን ኢዜአ ዘግቧል ፡፡

ተመሳሳይ ልጥፎች

በቶኪዮ ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀንቷቸዋል

admin

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ በበርሚንግሃም የ3 ሺህ ሜትር የቤት ውስጥ ሩጫ አሸነፈች

admin

አስተያየት ይስጡ