
አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ (ኤ ኤም ኤን) ሀምሌ 23/2015 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት “በቴክኔክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጆቻችን በተለያዩ የሙያ መስኮች ያሰለጠናችውን 6244 ተመራቂዎች ዛሬ አስመርቀናል” ብለዋል።
ከንቲባዋ አያይዘውም የተመረቃችሁ ሰልጣኞችና ቤተሰቦቻቸው እንኳን ደስ ያላችሁ፤ ከተማችሁ ከናንት ብዙ ትጠብቃለችም ብለዋል።
ተመራቂዎች የቀሰማችሁትን ዕውቀትና ክህሎት ተጠቅማችሁ ከራሳችሁ አልፋችሁ ለሌሎች የስራ ዕድል የምትፈጥሩ፣ ተወዳዳሪና ጥራት ያለው ምርት በማምረት ሀገር የምታኮሩ ትጉህ ዜጋ ለመሆን በርትታችሁ ስሩም ብለዋል ከንቲባዋ በመልእክታቸው።