ሀሰተኛ ዶላር ለቪዛ አገልግሎት ክፍያ በመፈጸም የተጠረጠረ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ

You are currently viewing ሀሰተኛ ዶላር ለቪዛ አገልግሎት ክፍያ በመፈጸም የተጠረጠረ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ

AMN – መጋቢት 3/2017 ዓ.ም

ሀሰተኛ የአሜሪካ ዶላር ከትክክለኛው ጋር በመቀላቀል ለቪዛ አገልግሎት ክፍያ በመፈጸም የተጠረጠረን ግለሰብ በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያደረገ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ።

ተጠርጣሪው ድርጊቱን የፈጸመው የካቲት 29 ቀን 2017 ዓ.ም በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 ጎተራ አካባቢ ከሚገኘው የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት መስሪያ ቤት ውስጥ መሆኑ ተገልጿል።

ተጠርጣሪው 3 ሺህ 500 ሀሰተኛ ዶላር ከትክክለኛ 3 ሺህ 250 የአሜሪካ ዶላር ጋር በመቀላቀል ለቪዛ አገልግሎት ክፍያ ለመፈጸም ሲሞክር በመስሪያ ቤቱ ሰራተኞች እጅ ከፍንጅ መያዙ ተመላክቷል።

ፖሊስ ተጠርጣሪውን በቁጥጥር ስር ካዋለ በኋላ የሰው እና የሰነድ ማስረጃዎችን በማሰባሰብ ተገቢውን የምርመራ ስራ እያከናወነ መሆኑንም ገልጿል።

የውጭ ሀገራትንም ሆነ የኢትዮጵያን ብር እያባዙ ሀሠተኛ ገንዘቦችን ወደ ተቋማት እና ህብረተሰቡ ማሰራጨት እና መገልገል የከፋ ጉዳት እንደሚያስከትል የገለጸው ፖሊስ፣ በእንደዚህ ዓይነት ተግባር ላይ የተሰማሩ አካላት ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ ማሳሰቡን ከአዲስ አበባ ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review