ሀገርን ለማጽናት ችግኝ መትከል እና መንከባከብ የትውልዱ አደራ ነው፡- ዘላለም ሙላቱ (ዶ/ር)

You are currently viewing ሀገርን ለማጽናት ችግኝ መትከል እና መንከባከብ የትውልዱ አደራ ነው፡- ዘላለም ሙላቱ (ዶ/ር)

ሀገርን ለማጽናት ችግኝ መትከል እና መንከባከብ የትውልዱ አደራ ነው፡- ዘላለም ሙላቱ (ዶ/ር)

AMN- ሐምሌ 12/2016 ዓ.ም

ሀገርን ለማጽናት ችግኝ መትከል እና መንከባከብ የትውልዱ አደራ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዘላለም ሙላቱ(ዶ/ር) ገለጹ፡፡

የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሄራዊ ፈተና ያጠናቀቁ ተማሪዎች እና የትምህርት ዘርፍ ባለድርሻ አካላት በእንጦጦ ፓርክ አረንጓዴ አሻራቸውን አኑረዋል፡፡

ችግኝ መትከል የሁሉም ሰው ኃላፊነት ሊሆን እደሚገባ የጠቀሱት ተማሪዎቹ በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ችግኝ በመትከል እና በመንከባከብ አረንጓዴ ሃገርን መፍጠር ላይ ተማሪዎች በስፋት ሊሳተፉ እንደሚገባ አመልክተዋል፡፡

በአረንጓዴ የተሸፈነች እና ከአየር ብክለት የጸዳች ሀገር እና ከተማን ለትውልድ ለማውረስ በሚደረገው ጥረት ውስጥ ነገ የሀገር ተረካቢ የሆኑ ትውልዶችም አሻራቸውን እያኖሩ ነው ተብሏል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ትምህት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ፣ችግኝ መትከል መንከባከብ እና ማሻገር የትውልድ አደራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ይህን መሰረት በማድረግ ከሁሉም ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ የ12ኛ ክፍል መለልቂያ ብሄራዊ ፈተና ተፈታኞች በአረንጓዴ አሻራ ውስጥ እንዲሳተፉ መደረጉን እና ይህም አደራ የተላለፈበት መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የጉለሌ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ወልዴ ወጌሳ በዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሃግብር በክፍለ ከተማው 1ነጥብ 5 ሚሊየን ችግኝ ለመትከል ታቅዶ እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰው በዛሬው እለት የ12ኛ ክፍ ፈተና ያጠናቀቁ ተማሪዎች እና የፈተና አስፈጻሚዎች ያከናወኑት የችግኝ ተከላ እቅዳቸውን ከግብ ለማድረስ የሚረዳ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ሰሞኑን የ12ኛ ክፍል ፈተናን በመውሰድ ያሳለፉ እና ዛሬ ላይ የተሻለች ሃገርን ለመረከብ ይረዳ ዘንድ እየተከናወነ በሚገኘው የአረንጓዴ አሻራ መረሃብር ላይ ሲሳተፉ የነበሩ ተማሪዎች በበኩላቸው ችግኝ መትከል የሁሉም ሰው ኃላፊነት ሊሆን እደሚገባ ጠቅሰው በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ችግኝ በመትከል እና በመንከባከብ አረንጓዴ ሃገርን መፍጠር ላይ ተማሪዎች በስፋት ሊሳተፉ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

የ12ኛ ክፍል ፈተናን ሲያስፈጽሙ የነበሩ እና በመረሃግብሩ ላይ የተሳተፉ መምህራን ነገን ታሳቢ ተደርገው የሚከናወኑ የልማት ስራዎች በራሳቸው በነገ ተረካቢ ትውልዶች አጅ እንዲፈጸም መደረጉ ትልቅ ትርጉም አለው ብለዋል፡፡

የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሄራዊ ፈተና ያጠናቀቁ ተማሪዎች እና ፈተናውን ያስፈጸሙ ፈታኞች እዲሁም የተለያዩ ባለድርሻ አካላት የእንጦጦ ፓርክን ጎብኝተዋል፡፡

በሀብታሙ ሙለታ

#Addisababa

#Ethiopia

ትክክለኛውን የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዲጂታል ሚዲያ የትስስር አውታሮችን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑን!

https://linktr.ee/AddisMediaNetwork

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review