AMN – ጥቅምት 14/ 2017 ዓ.ም
ህብረተሰቡን ያሳተፉ ስራዎች በመሰራታቸዉ ከተማዋ ሰላምና ጸጥታዋ የተረጋገጠ እና ለኑሮ ምቹ እንድትሆን ማስቻሉን የሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ አስታወቀ ።
ቢሮዉ የበጀት አመቱን ሩብ አመት አፈጻጸም ከህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ ጋር ገምግሟል ።
የቢሮዉ ምክትል ሃላፊ አቶ ሚደቅሳ ከበደ ቢሮው 11 ሺህ ወጣት የሰላም ሰራዊት አሰልጥኖ ከነባር የሰላም ሰራዊት ጋር እንዲቀላቀሉ ማድረጉን ፣ በከተማዋ የጫኝ እና አዉራጆችን አሰልጥኖ ወደ ስራ ማስገባቱን ተናግረዋል ።
ከአንድ ሚሊየን በላይ የሚሆኑ የህብረሰብ ክፍሎችን በሰላም ዙሪያ ማወያየቱ በሩብ አመቱ ከነበሩ አንኳር ተግባራት መካከል መሆናቸዉን አንስተዋል ።
በተለይ ህብረተሰቡን ያማከሉ በርካታ ተግባራት መተግበራቸዉ የአዲስ አበባን ሰላም ማጠናከር ተችሏልም ብለዋል ።
የበጀት አመቱ ሩብ አመት በከተማዋ በርካታ የአደባባይ በአላትንና አለም አቀፋዊ ጉባኤዎችን ያለምንም የጸጥታ ችግር ያከናወነችበት እንደነበርም አንስተዋል ምክትል ቢሮ ሃላፊዉ ።
ለዚህ ስኬት የህብረተሰብ አደረጃጀት የአንበሳዉን ድርሻ ተወጥቷልም ብለዋል ።
በአለማየሁ አዲሴ