ህዝበ ሙስሊሙ የኢድ አል አድሃ (አረፋ) በዓልን ሲያከብር የተቸገሩ ወገኖችን በመደገፍ ሊሆን ይገባል

You are currently viewing ህዝበ ሙስሊሙ የኢድ አል አድሃ (አረፋ) በዓልን ሲያከብር የተቸገሩ ወገኖችን በመደገፍ ሊሆን ይገባል

AMN ግንቦት 29/2017

ህዝበ ሙስሊሙ የኢድ አል አድሃ (አረፋ) በዓልን ሲያከብር የተቸገሩ ወገኖችን የመደገፍ ስራ ማጠናከር እንዳለበት በአሶሳ ከተማ የሚገኙ የእምነቱ ተከታዮች ተናገሩ።

1 ሺህ 446ኛው የኢድ አል አደሃ አረፋ በዓል በአሶሳ ከተማ በተለያዩ ሃይማኖታዊ ስርዓቶች እየተከበረ ይገኛል።

በበዓሉ ላይ ኢዜአ ያነጋገራቸው የእምነቱ ተከታዮች እንደተናገሩት የአረፋ በዓል አቅመ ደካሞች የሚደገፉበት እና በመተጋገዝ የሚከበር በዓል ነው ብለዋል።

ለበዓሉ ከሚያከናውነው እርድ ለአቅመ ደካሞች በማካፈል በዓሉን ተደስተው እንዲያሳልፉ እንደሚያደርግ የገለጸው ሱሌማን አብዱላሂ ነው።

በዓሉን ከተቸገሩ ወገኖች ጋር ማሳለፍ ለህሊና ከሚሰጠው ደስታ በተጨማሪ በእምነቱ ዘንድ የሚወደድ ተግባር እንደሆነ ገልጸዋል።

ሌላዋ የአሶሳ ከተማ ነዋሪ ዳረሰላም ዘሪሁን በበኩሏ፥ የአረፋ በዓል ለየት የሚያደርገው በሚከናወነው እርድ መሆኑን ገልፃ ጸ በዓሉን ቤተሰብ እና ዘመድ በመጠየቅ በጋራ እንደሚያሳልፉ ተናግራለች።

የአረፋ በዓል ህዝበ ሙስሊሙ የመረዳዳት ባህሉን የሚያጠናክርበት፣ አቅመ ደካሞችን የሚያግዝበት ታላቅ በዓል ነው ያሉት ደግሞ ኡስታዝ ዘይኑ ፋሪስ ናቸው።

በዓሉ ሃይማኖታዊ ስርዓቶች የሚከናወኑበት ከዘመድ ወገኖች ጋር በአንድነት የምናከብረው ነው ብለዋል።

የአሶሳ ከተማ ከንቲባ አብዱልከሪም አብዱራሂም በበኩላቸው፥ የከተማዋ ነዋሪዎች በበዓሉ ወቅት የሚያሳዩትን መደጋገፍ ባህል በማድረግ የተቸገሩ ወገኖችን መደገፍ ይገባል ነው ያሉት።

የከተማ አስተዳደሩ ለአቅመ ደካሞች ድጋፍ በማድረግ በዓሉን በደስታ እንዲያሳልፉ ማድረጉንም ጠቅሰዋል።

1 ሺህ 446ኛው የኢድ አል አደሃ በዓል በአሶሳ ከተማ በርካታ የእምነቱ ተከታዮች በተገኙበት በኢድ ሶላት ተከብሯል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review