ለሀገራዊ ምክክር ሂደቱ የኃይማኖት ተቋማት ሚና በእጅጉ የጎላ ነው፡- የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን

You are currently viewing ለሀገራዊ ምክክር ሂደቱ የኃይማኖት ተቋማት ሚና በእጅጉ የጎላ ነው፡- የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን

AMN- መስከረም 28/2017 ዓ.ም

ለሀገራዊ ምክክር ሂደቱ የኃይማኖት ተቋማት ሚና በእጅጉ የጎላ መሆኑን የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የኃይማኖት ተቋማትን ሚና እና ተሳትፎ በሀገራዊ ምክክር ሂደቱ ለማጎልበት ያለመ ውይይት አካሂዷል፡፡

ኮሚሽኑ ዛሬ በአዲስ አበባ ባዘጋጀው የውይይት መድረክ የኃይማኖት ተቋማት ጉባኤ አባላትና በጉባኤው በአባልነት ያልተመዘገቡ የኃይማኖት ተቋማት ተሳትፈዋል፡፡

የውይይት መድረኩን በንግግር የከፈቱት የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር መስፍን አርአያ (ፕሮፌሰር) ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር ኮሚሽኑ ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ የኃይማኖት ተቋማት ሚና ለሀገራዊ ምክክር ሂደቱ በእጅጉ የጎላ እንደነበር አውስተዋል።

የኃይማኖት ተቋማቱ ኮሚሽኑ የተሳታፊዎችን ልየታ ባከናወነበት ወቅት የኮሚሽኑ ተባባሪ አካል በመሆን ላበረከቱት በጎ አስተዋፅኦ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ተቋማቱ በአጀንዳ ልየታ ሂደት ላይ ተሳትፎ በማድረግ፣ የምክክር ሂደቱ ስኬታማ እንዲሆን በፀሎት በማገዝ እንዲሁም ለየእምነቱ ተከታይ ስለ ሀገራዊ ምክክሩ ግንዛቤ በማስጨበጥ ረገድ ያበረከቱትን አስተዋጽኦ አወድሰዋል።

በውይይቱ ላይ ኮሚሽኑ በእስከዛሬ ጉዞው የሰራቸውን አበይት ተግባራት አቅርቦ ሀሳብና እና አስተያየቶችን ከተሳታፊዎቹ ወስዷል፡፡

ወደፊት በጋራ ሊከናወኑ የሚገባቸውን ተግባራት የጋራ ግብረ-ሀይል በማቋቋም በትብብር ለመስራት ስምምነት ላይ መደረሱን ከኮሚሽኑ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review