AMN – መስከረም 29/2017 ዓ.ም
በኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት አዘጋጅነት ዘንድሮ ለሦስተኛ ጊዜ የተዘጋጀው ፓን አፍሪኮን ኤ.አይ 2024 ኮንፍረንስ ማብቂያውን ዛሬ አድርጓል፡፡
በዓድዋ ድል መታሰቢያ ለሁለት ቀናት ሲካሄድ በቆየው ኮንፍረንስ ላይ ከ1500 በላይ ተሳታፊዎች ታድመውበታል፡፡
በሁለቱ ቀናት የኮንፍረንሱ ቆይታ 24 የጥናታዊ ጽሁፎች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡
በኮንፍረንሱ ላይ የመዝጊያ ንግግር ያደረጉት የተለያዩ ምርምሮችን በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዙሪያ የሚያካሂዱትና ተቋማትን የሚመሩት የሃውክ ዩኒቨርሲቲው ፕሮፌሰር ዶ/ር አኪም ኢቤንታል፣ በመሰል ኮንፍረንሶች ወጣቶች መሳተፋቸው በዘርፉ መሠረት የሚጥልና ለአህጉሪቱም መልካም እድልን የሚፈጥር መሆኑን ገልጸዋል፡፡

አፍሪካ በመጪዎቹ ዓመታት በዘርፉ ፍሬያማ የምትሆንበት እንደሚሆንም ጠቁመዋል፡፡
ለመርሓ ግብሩ መሳካት አስተዋጽኦ ለነበራቸው አካላት ምስጋና ማቅረባቸውን የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት መረጃ ያሳያል፡፡
በመዝጊያ ሥነ ስርዓቱ ላይ በኮንፍረንሱ በተዘጋጀው የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዘርፍ ተመራማሪዎች እና የፈጠራ ሀሳብ ያላችው የዘርፉ አንቀሳቃሾች ውድድር አሸናፊ ለሆኑ የማበረታቻ የገንዘብ ሽልማት ተበርክቷል፡፡