ለሚ ናሽናል ሲሚንቶ 44 የጭነት ከባድ ተሸከርካሪዎችን ወደ አገር ውስጥ አስገባ

You are currently viewing ለሚ ናሽናል ሲሚንቶ 44 የጭነት ከባድ ተሸከርካሪዎችን ወደ አገር ውስጥ አስገባ

AMN- ጥቅምት 24/2017 ዓ.ም

ለሚ ናሽናል ሲሚንቶ ወደ ሀገር ከሚያስገባቸው 330 ገልባጭና የጭነት ከባድ ተሸከርካሪዎች 44ቱ ለሚ ከተማ ደረሱ።

ለሚ ናሽናል ሲሚንቶ ፋብሪካ በሦስተኛ ዙር 44 ገልባጭ ከባድ ተሸከርካሪዎችን ወደ ሀገር ውስጥ ማስገባቱ ተገልጿል፡፡

ኩባንያው ወደሀገር ውስጥ እያስገባቸው ከሚገኙት 330 ገልባጭና የጭነት ከባድ ተሸከርካሪዎች መካከል በመጀመሪያ ዙር 36፣ በሁለተኛው ዙር 30 ተሸከርካሪዎችን በሰሜን ሸዋ ዞን እንሳሮ ወረዳ ለሚ ከተማ መግባታቸው ይታወቃል፡፡

በሦስተኛ ዙር ደግሞ 44 ተጨማሪ ገልባጭ ከባድ ተሸከርካሪዎች ለሚ ናሽናል ሲሚንቶ ፋብሪካ በመግባት ላይ ይገኛሉ፡፡

እነዚህ ከባድ ተሽከርካሪዎች የሲሚንቶ ምርት ግብዓት የሆነውን ማዕድን ከማምረቻ ጣቢያው ማከማቻ ቦታ የሚያጓጉዙ እጅግ ግዙፍና ዘመናዊ የሆኑ ገልባጭ ከባድ ተሸከርካሪዎች መኾናቸውን ተመልክቷል።

ለሚ ናሽናል ሲሚንቶ ፋብሪካ ከጥቅምት 21 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ምርቱን ለገበያ ማቅረብ መጀመሩን ማስታወቁ ይታወሳል ሲል አሚኮ ዘግቧል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review