
AMN- ጥቅምት 28/2017 ዓ.ም
በ6ኛ ዕዝ የአንድ ኮር አባላት ከህብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ ለአሸባሪው የሸኔ ቡድን ሊተላለፉ የነበሩ የመገናኛ ራዲዮኖችን በቁጥጥር ስር አውለዋል።
መነሻውን አዲስ አበባ አድርጎ አሊ ዲሮ ወደተባለ ቦታ ለአሸባሪው ቡድን ሊደርስ የነበረ 21 ዘመናዊ የመገናኛ ራዲዮን በሰሜን ሸዋ ዞን ፊቼ ከተማ የኮሩ አባላት ባደረጉት ብርቱ ክትትል በቁጥጥር ስር ማዋል መቻሉን የኮሩ ዘመቻ ሃላፊ ሌተናል ኮሎኔል ጌታሁን ደምሴ ተናግረዋል፡፡

የሽብር ቡድኑ በወሊሶ ወረዳ ቀብሮት የነበረ 2 ክላሽ ከ280 ጥይት ጋር በተመሳሳይ ጥቆማ መያዙን የተናገሩት ሃላፊው በአካባቢው እየተንቀሳቀሱ የሚገኙት የአሸባሪው ሸኔ ቡድንና ግብረ አበሮቹ በህገወጥ መንገድ እያደረጉት ያለው ተግባር የሀገርን የልማት እንቅስቃሴ ለማደናቀፍ ያለመ ነው ማለታቸውን ከመከላከያ ሰራዊት የማህበራዊ ትስስር ገጽ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
ትክክለኛውን የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዲጂታል ሚዲያ የትስስር አውታሮችን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑን!