AMN- ጥቅምት 30/2017 ዓ.ም
ለከተማዋ ሠላም ፖሊሳዊ ስነምግባር በመላበስ፣ የሌሊት ቁርና የቀትር ጸሐይን በመቋቋም በሰብዓዊነትና በጀግንነት እስከ ህይወት መስዋእትነት በማገልገል በተሰራዉ ስራ እና በተገኘዉ ዉጤት የተሻለ አፈጻጸም ላስመዘገቡ የከተማዋ ፖሊስ ሠራዊት አባላት ዕውቅና ሰጥተናል ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡
ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባስፈሩት መልዕክት “ከአዲስ አበባ ፖሊስ ጋር በቅርበት በመስራት ከተማችን ፍጹም ሰላማዊ እንድትሆን እና ሰላምና ደህንነትን ለማረጋገጥ እየሰራችሁ ለምትገኙ የጸጥት አካላት በሙሉ ላደረጋችሁት አስተዋፅዖ ላመሰግናችሁ እወዳለሁ” ብለዋል።