AMN – ጥቅምት 14/ 2017 ዓ.ም
በአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን በ40/60 የቤቶች ልማት ፕሮግራም በተለያዩ ሳይቶች ለተገነቡ የጋራ መኖሪያ ቤቶች የሚሆኑ የውሃ ፓምፖች በዛሬው ዕለት አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡
ፓምፖቹበኮርፖሬሽኑ ስር በሚገኘው የበሻሌ ሳይት ገብተዋልም ተብሏል፡፡
ፓምፖቹ በ40/60 የቤቶች የነበረውን የውሀ አቅርቦት ችግር ይፈታሉ ተብሎ ይጠቃል፡፡
በቅርቡ ፓምፖቹ ወደ ሥራ ገብተው አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምሩ ከአዲስ አበባ ቤቶች ልማት አስተዳደር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡