ለ8 ሳምንታት በማህበረሰቡ ውስጥ ባካሄዱት ጤና ነክ ጥናት ለተለያዩ ችግሮች መፍትሄ መስጠታቸውን ዕጩ ተመራቂ የጤና ሳይንስ ተማሪዎች ገለጹ

AMN ህዳር 19/2017 ዓ.ም

የዳግማዊ ምኒሊክ ሆስፒታል ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የተማሪዎች የቡድን ተግባር ስልጠና ማጠቃለያ መርሃ ግብር አካሄዷል።

ኮሌጁ በተግባር የተደገፈ ትምህርት ለተማሪዎች እየሰጠ የቆየ ሲሆን ተማሪዎችም የተለያዩ ባለሃብቶችን በማስተባበር ወደ ማህበረሰቡ በመውረድ ችግር ፈቺ ተግባራትን በተጨባጭ ማከናወናቸው ተብራርቷል።

በተማሪዎቹ ከተከናወኑ ተግባራት መካከል በየካ ጤና ጣቢያ ለአካል ጉዳተኞች መንገድ ተሰርቷል።

በስብዕና መገንቢያ ማዕከላት እና በጤና ተቋማት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች ስለመስራታቸው ተብራርቷል።

በሚኪሊላንድ ጤና ጣቢያ እና በትምህርት ቤቶች ላይ ለ8 ሳምንታት ባደረጉት ጥናት የተለያዩ አዎንታዊና አሉታዊ ነገሮችን በመለየት ለችግሮች መፍትሄ መስጠታቸውን ተማሪ ኦሊያድ ተካልኝ ተናግሯል።

የዳግማዊ ምኒሊክ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ዋና ዳይሬክተር አቶ አለሙ ዳንኤል ኮሌጁ ላለፉት 75 ዓመታት የመማር ማስተማር ሂደት ላይ ፈር ቀዳጅ ሚና ሲወጣ መቆየቱን ጠቅሰው ዕጩ ተመራቂ ተማሪዎቹ ያካሄዱት ማህበረሰብ አቀፍ ጥናት ለጤናው ዘርፍ ትልቅ ግብአት ይሆናል ብለዋል።

የሆስፒታሉ ጤና ሳይንስ ከ18 በላይ የመደበኛ እና ከ8 በላይ የድህረ ምረቃ ትምህርት እንደዚሁም አጫጭር ስልጠናዎችን በመስጠት ላይ እንደሚገኝም ተገልጿል።

በምትኩ ተሾመ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review