ልዩ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው የማህበረሰብ ክፍሎች ተሳትፎና ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ በትኩረት እየተሠራ ነው-ሴቶች ህጻናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ

You are currently viewing ልዩ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው የማህበረሰብ ክፍሎች ተሳትፎና ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ በትኩረት እየተሠራ ነው-ሴቶች ህጻናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ

AMN – ጥቅምት 07/2017 ዓ.ም

ልዩ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው የማህበረሰብ ክፍሎች ተሳትፎና ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ በትኩረት እየተሠራ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሴቶች ህጻናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ አስታውቋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሴቶች ህጻናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ከዩኒቨርሲቲዎች እና ከቴክኒክና ሙያ ትምህርት ኮሌጆች ተመርቀው የስራ ዕድል ያልተፈጠረላቸው ስራ ፈላጊ ወጣት ሴቶች በስራ ፈጠራ ዙሪያ ስኬታማ ሴቶች ተሞክሮአቸውንና የህይወት ልምዳቸውን የሚያካፍሉበት መድረክ አካሄዷል።

ቢሮው በየካ ክፍለ ከተማ ባካሄደው መድረክ ላይ ከአስራ አንዱም ክፍለ ከተሞች የተውጣጡ ስራ ፈላጊ ወጣት ሴቶች ተሳትፈዋል።

የአዲስ አበባ ሴቶች ህጻናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ወይንሸት ዘሪሁን ባደረጉት ንግግር፣ ቢሮው የሴቶችን የህጻናትን የአካል ጉዳተኞችን የአረጋውያንና ልዩ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው የማህበረሰብ ክፍሎች ተሳትፎና ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ በትኩረት እየሠራ መሆኑን ተናግረዋል።

በስልጠናው ላይ የተሳተፉት ወጣት ሴቶች የከተማ አስተዳደሩ ባመቻቸላቸው የስራ ዕድሎች ተደራጅተው በመስራት ራሳቸውንና ከተማቸውን ተጠቃሚ እንዲያደርጉም ነው የቢሮ ኃላፊዋ ጥሪ ያቀረቡት።

በመድረኩ ላይ በተለያዩ የሙያ ዘርፎች ላይ የተሠማሩና በተሠማሩበት ዘርፍም ስኬታማ የሆኑ ስራ ፈጣሪ ሴቶች የሕይወት ልምዳቸውንና የስኬት መንገድ ተሞክሯቸውን ለወጣቶቹ አካፍለዋል።

በምትኩ ተሾመ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review