በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ በመርካቶ እና በመሳለሚያ አካባቢ በመንገድ ላይ ሽንት በመሽናት አካባቢ በማቆሸሽ ደንብ የተላለፉ 50 ግለሰቦች እያንዳንዳቸውን 2000 ብር በድምሩ 100,000/አንድ መቶ ሺህ/ ብር የገንዘብ ቅጣት በመቅጣት አስተዳደራዊ እርምጃ መውሰዱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን አስታውቋል፡፡
ባለስልጣኑ በደንብ ቁጥር 167/2016 ላይ ለህብረተሰቡ በተለያዩ አግባቦች ሰፊ የግንዛቤ ስራ መስራቱን የገለጸ ሲሆን ደንብ በሚተላለፉ ግለሰቦች ላይ የሚወስደውን እርምጃ አጠናክሮ እንደሚቀጥል በማኅበራዊ ትስስር ገጹ አስታውቋል።