በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ ቢሮ የሃይማኖትና ሰላም እሴት ግንባታ ዘርፍ የተዘጋጀው “የመንግስትና የሃይማኖት ተቋማት ግንኙተንና ትብብር” መድረክ እየተካሄደ ነው።
በመድረኩም መንግስት ለጀመራቸው የልማት እና የሰላም እሴት ግንባታ ሀገራዊ አጀንዳዎች፣ የሃይማኖት ተቋማት በላቀ ግንኙነት እና ትብብር ድጋፋቸውን አጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባ ተመላክቷል።
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ጫኔ፣ የሃይማኖት ተቋማት ለልማት እና ለሰላም እሴት ግንባታ እያበረከቱት የሚገኘውን የማይተካ ሚና አጠናክረው እንዲቀጥሉ አስገንዝበዋል።
በአዲስ አበባ ከተማ በሃይማኖት ተቋማት እና በመንግስት መካከል ያለው ትብብር ማህበራዊ ደህንነትን ሰላምና ልማትን በማጎልበት በኩል ትልቅ ሚና በመጫወት ላይ ይገኛልም ብለዋል፡፡

ይህ አጋርነትም የህብረተሰቡን ተግዳሮቶች ለመፍታትና ሀገራዊ የልማት አጀንዳዎችን ለማስፈፀም ጉልህ ሚና አለው ሲሉ አክለዋል።
በዚህ መድረክም በኢትዮጵያ ሀገረ መንግስት ግንባታ ሂደት ውስጥ የሃይማኖት ተቋማት ሚና እንዲሁም የቀጣይ ትብብርና ግንኙነቶችን የተመለከተ የመነሻ ፅሁፍ ቀርቦ ውይይት እየተደረገበት ይገኛል።
በይታያል አጥናፉ