መንግስት የኃይል ልማት ዘርፍ ሪፎርምን በመተግበር የግሉን ዘርፍ ተሳትፎ ለማሳደግ እየሰራ ነው – ኢንጂነር ሱልጣን ወሊ (ዶ/ር)

You are currently viewing መንግስት የኃይል ልማት ዘርፍ ሪፎርምን በመተግበር የግሉን ዘርፍ ተሳትፎ ለማሳደግ እየሰራ ነው – ኢንጂነር ሱልጣን ወሊ (ዶ/ር)

AMN- ጥቅምት 30/2017 ዓ.ም

መንግስት የኃይል ልማት ዘርፍ ሪፎርምን በመተግበር የግሉ ዘርፍ በመስኩ ያለውን ተሳትፎ ለማሳደግ እየሰራ እንደሚገኝ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ገለጸ።

የጣልያን ባንክ እና የጣልያን ኢኮኖሚና ፋይናንስ ሚኒስቴር ከዓለም ባንክ ጋር በመተባበር ያዘጋጁት የከፍተኛ አመራሮች ጉባኤ በሮም እየተካሄደ ነው።

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ዴኤታ ኢንጂነር ሱልጣን ወሊ (ዶ/ር) በጉባኤው ላይ እየተሳተፉ ይገኛሉ።

ጉባኤው በአፍሪካ ሁሉን አቀፍ ዕድገትን ለማረጋገጥ የሚረዱ የኢነርጂ አማራጮች ላይ ትኩረት ያደረገ መሆኑ ተገልጿል።

ሚኒስትር ዴኤታው በጉባኤው ላይ ተመጣጣኝ፣ አስተማማኝና ዘላቂ የኢነርጂ አቅርቦትን በአፍሪካ ለማስፋፋት የሚረዱ የስትራቴጂ አማራጮችን አስመልክቶ ሀሳብ አቅርበዋል።

በዓለም ባንክ የፋይናንስ ድጋፍ የብሔራዊ ኤሌክትሪፊኬሽን ኘሮግራም እየተተገበሩ ስላሉ ኘሮጀክቶችም ገለጻ አድርገዋል።

በኢትዮጵያ ባለፉት ስድስት እና ሰባት ዓመታት የኤሌክትሪክ ኃይል ልማትና ተደራሽነትን ለማረጋገጥ ሰፋፊ ስራዎች መከናወናቸውን ገልጸዋል።

መንግስት የኃይል ልማት ዘርፍን ለማስፋፋት የግሉን ዘርፍ ተሳትፎ ለማሳደግ የኃይል ዘርፍ ማሻሻያ እንዲሁም ከሪፎርሙ የሚመነጩ የፖሊሲ ማሻሻያዎችና ማበረታቻዎችን እየተገበረ እንደሚገኙ አመልክተዋል።

ኢነርጂ ለኢኮኖሚ ልማት ብሎም ለዜጎች ኑሮ መሻሻልና ሁለንተናዊ ብልፅግና ያለውን አስተዋፅኦ ወሳኝ መሆኑንም አንስተዋል።

የኃይል ዘርፍ ልማት ከፍተኛ ካፒታል ፍሰትን የሚፈልግ በመሆኑ ዘርፉን በይበልጥ ለግሉ ዘርፍ ክፍት በማድረግ ምቹ ሁኔታዎችን የመፍጠር ሥራዎች መከናወናቸውን አብራርተዋል።

የመንግስት እና የግል አጋርነት ማዕቀፍ ዝግጅት እና ዘርፉን ለቢዝነስ ምቹ የማድረግ ስራዎች መከናወናቸውን አመልክተዋል።

በተጨማሪ የኃይል ልማት ዘርፍ ሪፎርምን በሥራ ላይ በማዋል መስኩን ይበልጥ ለግሉ ዘርፍ ተሳትፎ ምቹ እንዲሆን እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰው፤በዚህ ረገድ የልማት አጋሮች ሚና ወሳኝ እንደሆነ አንስተዋል።

በተለይም በዓለም ባንክ ድጋፍ እየተተገበሩ ባሉ የብሔራዊ ኤሌክትሪፊኬሽን ኘሮግራምና በኢትዮጵያ የኤሌክትሪክና የመብራት ስርጭትን ተደራሽ የማድረግ ፕሮግራም ላይ የግሉን ዘርፍ ተሳትፎ ለማሳደግ እየተሰራ ነው ብለዋል።

የግሉ ዘርፍ በኃይል ልማት ዘርፍ ሪፎርም እና ዘላቂና ንጹህ የኃይል ትራንስፎርሜሽንን ማፋጠን ማዕቀፎች ላይ ያለው ድርሻ ለመጨመር እየተሰራ እንደሚገኝ ሚኒስትር ዴኤታው መግለጻቸውን ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review