መንግስት የዜጎችን ጥያቄ ለመመለስ የተለያዩ ህዝባዊ ውይይቶችን በማድረግ እና በመቀራረብ እየሰራ ነው-አቶ ሞገስ ባልቻ

You are currently viewing መንግስት የዜጎችን ጥያቄ ለመመለስ የተለያዩ ህዝባዊ ውይይቶችን በማድረግ እና በመቀራረብ እየሰራ ነው-አቶ ሞገስ ባልቻ

AMN-የካቲት 15/2017 ዓ.ም

2ኛው የብልጽግና ፓርቲ መደበኛ ጉባኤ ውሳኔዎች እና አቅጣጫዎች ዙሪያ ያተኮረ የውይይት መድረክ ከአዲስ አበባ ነዋሪዎች ጋር እየተካሄደ ነው።

በውይይት መድረኩ የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳደር እና የብልጽግና ፓርቲ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ወይዘሮ አለሚቱ ኡሙድ፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳደር እና የብልጽግና ፓርቲ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ዶክተር እንዳሻው ጣሰው፣የአዲስ አበባ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ እና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም በርካታ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች እየተሳተፉ ይገኛሉ።

በውይይት መድረኩ የ2ኛው የብልጽግና ፓርቲ መደበኛ ጉባኤ ውሳኔዎች እና አቅጣጫዎች እንዲሁም ባለፉት አመታት በመዲናዋ የተከናወኑ የልማት ስራዎችን የተመለከተ ለውይይት የቀረበ ጽሁፍ በአዲስ አበባ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ አማካኝነት ቀርቧል።

አቶ ሞገስ በዚሁ ወቅት እንዳሉት መንግስት የዜጎችን ጥያቄ ለመመለስ የተለያዩ ህዝባዊ ውይይቶችን በማድረግ እና በመቀራረብ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

በከተማዋ ውስጥ ሁሉንም ነዋሪ ያቀፈ የልማት ስራ መከናወኑን የገለጽት ኃላፊው ባለፉት 3 አመታት ለ1.2 ዜጎች ቋሚ የስራ ዕድል መፈጠሩንም ተናግረዋል።

በሌሎች የልማት ዘርፎችም አመርቂ ውጤቶች መገኘታቸውን ጠቁመዋል።

በመሰረተ ልማት ዘርፍ በርካታ ስራዎች ቢሰሩም ከፍላጎት አንጻር በቀጣይ በትኩረት ይሰራበታልም ብለዋል።

የብልጽግና ፓርቲ ከቃል እስከ ባህል በሚል መሪ ሀሳብ 2ኛ መደበኛ ጉባኤውን ማካሄዱ ይታወሳል።

በሃብታሙ ሙለታ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review