መከላከያ የኢትዮጵያን ዳር ድንበር እና ብሔራዊ ጥቅም ለማስከበር ከመቼውም ግዜ በላይ ዝግጁ ነው፡-ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ

You are currently viewing መከላከያ የኢትዮጵያን ዳር ድንበር እና ብሔራዊ ጥቅም ለማስከበር ከመቼውም ግዜ በላይ ዝግጁ ነው፡-ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ

AMN- ጥቅምት 15/2017 ዓ.ም

ወቅቱ የሚጠይቀውን ቁመና ይዞ የተገነባው የመከላከያ ሀይል የኢትዮጵያን ዳር ድንበር እና ብሔራዊ ጥቅም ለማስከበር ከመቼውም ግዜ በላይ ዝግጁ መሆኑን የጦር ሀይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ተናግረዋል።

117ኛው የሀገር መከላከያ ሰራዊት ቀን “በፈተናዎች ውስጥ እየተገነባ የመጣ ሰራዊት” በሚል መሪ ቃል ተከብሯል።

የጦር ሀይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ እንዳሉት የመከላከያ ሰራዊት ዝግጁነቱን አጠናክሮ ተልዕኮውን በብቃት እየተወጣ ይገኛል፡፡

መከላከያ ሰራዊቱ ጠላቶች የሚልኳቸውን የውስጥ ባንዳዎች በመቅጣት በሀገሪቱ የተሟላ ሰላም እያመጣ ይገኛልም ነው ያሉት።

የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ስምሪቶች በዝቶበት እንዲዳከም የተለያዩ ሴራዎች ቢሰሩበትም ሰራዊት በተለያዩ አውደ ውጊያዎች ከመዋጋት ግን ለጎን ራሱን እየገነባ የማይበገር የቀጠናው ሀይል ሆኖ ወጥቷል ነው ያሉት ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ።

ሰራዊቱ በስነ ልቦና ፣ በቴክኖሎጂ ፣ በትጥቅ ፣ በአደረጃጀት እና በመሳሰሉት መስኮች ተገንብቶ በአስተማማኝ ቁመና ላይ ይገኛል ያሉት ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በዚህ ረገድ የዛሬው ትውልድ ሀላፊነቱን ተወጥቷል፤ ቀጣዩ ትውልድም የሚረከበው የተገነባ ሰራዊት አዘጋጅቷል ብለዋል።

በሰብስቤ ባዩ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review