ማሰልጠኛ ትምህርት ቤቱ በዘመናዊ ወታደራዊ እውቀት ለሀገራቸው አስተማማኝ መከታ የሆኑ ወታደሮችን እያፈራ ነው:- ብርጋዴር ጀኔራል ጡምሲዶ ፊታሞ

You are currently viewing ማሰልጠኛ ትምህርት ቤቱ በዘመናዊ ወታደራዊ እውቀት ለሀገራቸው አስተማማኝ መከታ የሆኑ ወታደሮችን እያፈራ ነው:- ብርጋዴር ጀኔራል ጡምሲዶ ፊታሞ

AMN- መስከረም 30/2017 ዓ.ም

የጦላይ የባለሌላ ማዕረግተኛ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት በዘመናዊ ወታደራዊ እውቀት የላቀ ብቃት ተላብሰው ለሀገራቸው አስተማማኝ መከታ የሆኑ ወታደሮችን እያፈራ መሆኑን የትምህርት ቤቱ አዛዥ ብርጋዴር ጄኔራል ጡምሲዶ ፊታሞ ገለጹ።

የጦላይ የባለሌላ ማዕረግተኛ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት ሲያሰለጥናቸው የቆዩ መሰረታዊ ወታደሮችን አስመርቋል።

በምርቃት ስነስርዓቱ ላይ የመከላከያ ሎጂስቲክስ ዋና መምሪያ ኃላፊ ሌተናል ጄኔራል አብዱራህማን እስማኤልን ጨምሮ ሌሎችም ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖች ተገኝተዋል።

የጦላይ ባለሌላ ማዕረግተኛ ወታደራዊ ስልጠና ትምህርት ቤት አዛዥ ብርጋዴር ጀኔራል ጡምሲዶ ፊታሞ፤ ባደረጉት ንግግር ዘመናዊና የሰለጠነ ሰራዊት ለሀገር ህልውና ከመሆንም ባለፈ የተከበረውን ሙያ ለትውልድ ማሻገር የሚያስችል መሆኑን ገልጸዋል።

የጦላይ የባለሌላ ማዕረግተኛ ወታደራዊ ማሰልጠኛ በየጊዜው የሀገር አለኝታ የሆኑ የሰራዊት አባላትን በማፍራት በስኬት መንገድ ቀጥሎ እስካሁንም የዘለቀ መሆኑን ተናግረዋል።

በዛሬው እለትም በትምህርት ቤቱ የፕሮፌሽናል ወታደራዊ ስልጠና የወሰዱና ሀገራቸውን በላቀ ብቃት የሚያገለግሉ መሰረታዊ ወታደሮች ለምርቃት መብቃታቸውን ገልጸዋል።

መሰረታዊ ወታደሮቹ በስነ ልቦና ግንባታ፣የመከላከያ እሴቶች፣ የውጊያ እና ሌሎች ልዩ ልዩ ወታደራዊ ስልጠና የወሰዱ መሆናቸውን ጠቁመዋል።

በመሆኑም ወታደሮቹ የሀገር አስተማማኝ መከታ በመሆን የውጭም ይሁን የውስጥ ጠላትን በአስተማማኝ መልኩ የመመከት የላቀ ብቃት እንዳላቸውም ማረጋገጣቸውን ኢዜአ ዘግቧ ።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review