“ማይንቴክስ” የማዕድን እና የቴክኖሎጂ ኤክስፖ በህዳር ወር ይካሄዳል

You are currently viewing “ማይንቴክስ” የማዕድን እና የቴክኖሎጂ ኤክስፖ በህዳር ወር ይካሄዳል

AMN – መስከረም 14/2017 ዓ.ም

“ማይንቴክስ” የማዕድን እና የቴክኖሎጂ ኤክስፖ ከህዳር 14 እስከ 17 2017 ዓ.ም እንደሚካሄድ የማዕድን ሚኒስቴር አስታውቋል።

ኤክስፖው በርካታ አለም አቀፍ ኩባንያዎችን በማሳተፍ ለ 3 ኛ ጊዜ በሚሊኒየም አዳራሽ እንደሚካሄድ ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

እንዲሁም ኤክስፖውን ደረጃውን ከፍ አድርጎ በርካታ ኩባንያዎችን በማሳተፍ በድምቀት ለማካሄድ ዝግጅት መጠናቀቁ ተመላክቷል፡፡

በማዕድን እና በቴክኖሎጂ ዘርፍ የተሰማሩ ድርጅቶች በኤክስፖው ላይ በመሳተፍ ምርት እና አገልግሎታቸውን እንዲያስተዋውቁም ጥሪ ቀርቧል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review