ምክር ቤቱ አቶ ተስፋዬ ንዋይን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ አድርጎ ሾመ

You are currently viewing ምክር ቤቱ አቶ ተስፋዬ ንዋይን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ አድርጎ ሾመ

AMN – ሰኔ 05/ 2017 ዓ.ም

የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 36ኛ መደበኛ ስብሰባው አቶ ተስፋዬ ንዋይን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ አድርጎ ሾመ።

ምክር ቤቱ ዛሬ ባካሄደው 6ኛ ዙር 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን በ36ኛ መደበኛው ስብሰባው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የስራ አመራሮችን ሹመት መርምሮ አፅድቋል።

በዚህም አቶ ተስፋዬ ንዋይ የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ ፣ ወ/ሮ ነሲም አሊ እና አቶ ተክሊት ይመስል ደግሞ የምርጫ ቦርድ የስራ አመራር አባል አድርጎ ሾሟል።

በስብሰባ አጀንዳው፤ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ አመራሮች ሹመትን ከማፅደቅም በተጨማሪ የም/ቤቱን 4ኛ አመት የስራ ዘመን 35ኛ መደበኛ ስብሰባ ቃለ ጉባኤ ያፀደቀ ሲሆን፤ የኢትዮጵያ የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ረቂቅ አዋጅን እና የዕፅዋት ጥበቃና ኳራንታይን ረቂቅ አዋጅን መርምሮ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ መርቷል።

ራሄል አበበ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review