ምክር ቤቱ “የምትተክል ሀገር፣ የሚያፀና ትውልድ” በሚል መሪ ቃል የአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብር አካሄደ

You are currently viewing ምክር ቤቱ “የምትተክል ሀገር፣ የሚያፀና ትውልድ” በሚል መሪ ቃል የአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብር አካሄደ
  • Post category:ልማት

AMN – ሐምሌ 12/2016 ዓ.ም

የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና ጽ/ቤት አመራሮች እና ሠራተኞች በሀገር አቀፍ ደረጃ “የምትተክል ሀገር፣ የሚያፀና ትውልድ” በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ ባለው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብር የራሳቸውን አሻራ አስቀምጠዋል።

በመርሐ-ግብሩም የምክር ቤቱ ከፍተኛ አመራሮች፣ የምክር ቤት አባላት፣ የጽ/ቤቱ የሥራ ኃላፊዎች እና ሠራተኞች ተገኝተዋል።

መርሐ-ግብሩን የምክር ቤቱ ምክትል አፈ-ጉባኤ ወ/ሮ ሎሚ በዶ ያስጀመሩ ሲሆነ የችግኝ ተከላው በአራዳ ክፍለ ከተማ፣ ከአራት ኪሎ እስከ መገናኛ ባለው የኮሪደር ልማት፣ አዲስ በተዘጋጀው የቀበና አረንጓዴ አካባቢ ነው፤ በዕለቱም 3 ሺህ 600 ችግኞችም ተተክለዋል።

ምክር ቤቱ እና ጽ/ቤቱ ከረጅም ዓመታት ጀምሮ ይህን መርሐ-ግብር በየዓመቱ የሚያካሄድ መሆኑን ከምክር ቤቱ የተገኘው መረጃ ያመለክታል ይታወሳል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review