AMN- መስከረም 30/2017 ዓ.ም
6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ስብሰባውን እያካሄደ ነው፡፡
ምክር ቤቱ በስበሰባው የምክር ቤቱን 3ኛ አመት የስራ ዘመን 1ኛ አስቸኳይ ስብሰባ የኤሌክትሮኒክስ ፊርማ፣ የኢትዮጵያ የህንፃ ረቂቅ አዋጅ፣ የመድኃኒት ፈንድና የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎትን ለማቋቋም የቀረበ ረቂቅ አዋጅን መርምሮ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ እንደሚመራ ይጠበቃል፡፡
በተጨማሪም የጤና አገልግሎት አስተዳደር እና ቁጥጥር፤ እንዲሁም የሪል ስቴት ልማት እና የማይንቀሳቀስ ንብረት ግብይትና ግመታ ረቂቅ አዋጅን መርምሮ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ ይመራል ተብሎ እንደሚጠበቅ ከምክር ቤቱ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡