AMN- ጥቅምት 6/2017 ዓ.ም
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በኢትዮጵያ ኅብረት ሥራ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጌታቸው መለሰ(ዶ/ር) ህልፈት የተሰማቸውን ሀዘን ገልጸዋል።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት የኢትዮጵያ ኅብረት ሥራ ኮሚሽን ኮሚሽነር የነበሩት ጌታቸው መለሰ(ዶ/ር) በማለፋቸው የተሰማኝን ጥልቅ ኀዘን ለመግለጽ እወዳለሁ ብለዋል፡፡
ፈጣሪ ነብሳቸውን በአጸደ ገነት ያኑር ሲሉም ሀዘናቸውን ገልጸዋል።