ሦስተኛው የፓርላማ የዜጎች ፎረም “ሕገ መንግሥትና ሕገ መንግሥትታዊነት በኢትዮጵያ” በሚል የውይይት ርዕስ በመካሄድ ላይ ይገኛል።
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ እና ምክትል አፈ ጉባዔ፣ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባዔ፣ የመንግሥት ዋና ተጠሪ ሚኒስቴር፣ የምክር ቤቱ አባላት፣ ምሁራን እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።
በፎረሙ የኢትዮጵያ እና የዓለም ሕገ መንግሥቶች የታሪክ ጉዞ ላይ ያተኮሩ ፅሁፎች በመቅረብ ላይ ይገኛሉ።
የሕገ-መንግሥት ሪፎርም፣ የሕገ-መንግሥቱ ቅቡልነት እና ተግዳሮት ሀገራዊ መግባባት በኢትዮጵያ የሚዳስሱ ገለፃዎች በምሁራን በመቅረብ ላይ መሆናቸውን ከምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመለከታል።