AMN – መስከረም 23/2017 ዓ.ም
የኢሬቻ በዓልን አስመልክቶ “ኢሬቻ ለባህላችን ህዳሴ” በሚል መሪ ሀሳብ የባህል ፌስቲቫል በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለከተማ ተካሂዷል ።
የአዲስ አበባ ከንቲባ አማካሪ ዶ/ር ዳዲ ወዳጆ እንደገለጹት፣ ሰላም እና ፍቅር የሚንፀባረቅበትን የኢሬቻ በዓል በድምቀት ለማክበር አዲስ አበባ ተዘጋጅታለች፡፡
አቃቂ እና አካባቢው ለበዓሉ እንግዶች መውጪያ እና መግቢያ በመሆኑ የአካባቢው ነዋሪ እንግዶችን በመቀበል እና በማስተናገድ የተለመደውን ኢትዮጵያዊ ጨዋነቱን እንዲያሳይ ጠይቀዋል።
የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አለማየሁ ሚጀና፣ ኢሬቻ የኦሮሞ ብሔረሰብ ባህላዊ እሴቶች የሚንፀባረቅበት ታላቅ የአደባባይ በዓል መሆኑን በመግለጽ በዓሉ እሴቱን ጠብቆ እንደሚከበር ሁሉም ኃላፊነቱን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በፌስቲቫሉ ላይ የኦሮሞ ብሄር ማንነትን እንዲሁም ባህላዊ እሴትን የሚያሳዩ ባህላዊ ምግቦች እና ቁሳቁሶች ቀርበውበታል ።
በአለማየሁ አዲሴ