ሴቶች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን ለማስቆም ሁሉም የማህበረሰብ ክፍል አስፈላጊውን ትኩረት ሊያደርግ ይገባል፡- የአዲስ አበባ ሴቶች ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ

You are currently viewing ሴቶች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን ለማስቆም ሁሉም የማህበረሰብ ክፍል አስፈላጊውን ትኩረት ሊያደርግ ይገባል፡- የአዲስ አበባ ሴቶች ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ

AMN-ታህሳስ 1/2017 ዓ.ም

ሴቶች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን ለማስቆም ሁሉም የማህበረሰብ ክፍል አስፈላጊውን ትኩረት ሊያደርግ እንደሚገባ የአዲስ አበባ ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ አሳሰበ፡፡

ቢሮው “የሴቶች ጥቃት የእኔም ጥቃት ነው፤ ዝም አልልም” በሚል መሪ ቃል ለ19ኛ ጊዜ ሲካሄድ የቆየውን የፅረ ሴት ልጅ ጥቃት ንቅናቄ የማጠቃለያ መረሀ ግብር እያካሄደ ይገኛል፡፡

በመረሀ ግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ሴቶች ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ምክትል ሀላፊ ወይዘሮ ዝናሽ ከተማ በሴቶች ላይ የሚደርስ ፆታዊ ጥቃት የሰባዊ መብት ጥሰት መሆኑን በማንሳት ሁሉም የማህበረሰብ ክፍል አስፈላጊውን ትኩረት ሊሰጥና በቃ ሊል ይገባል ብለዋል፡፡

የፆታ ጥቃት የአንድ ሀገርን የማምረት አቅም የሚያዳክም እና የሴቶችን ተጠቃሚነት የሚያሳጣ መሆኑን የጠቀሱት ኃላፊዋ ከተማ አስተዳደሩ ከሚሰራቸው ስራዎች በተጨማሪ ሁሉም ዜጋ የሴት ልጅ ጥቃት የኔም ጥቃት ነው ማለት ይገባዋልም ብለዋል፡፡

በተለይም የሀይማኖት ተቋማት ላይ የሀይማኖት አባቶች ግንዛቤ በመፍጠር ረገድ የድርሻቸውን ሊወጡ እንደሚገባ ተጠቁማል፡፡

በመድረኩ የአዲስ አበባ ሴቶች ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ምክትል ሀላፊ ዝናሽ ከተማን ጨምሮ ባለድርሻ አካላት እና ከየቤተ -ዕምነቱ የተወጣጡ የሀይማኖት አባቶች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

በራሄል አበበ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review