ስፖርት ለዘላቂ ሰላም ግንባታ ያለውን ሚና ለማጎልበት እንሰራለን – የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር

You are currently viewing ስፖርት ለዘላቂ ሰላም ግንባታ ያለውን ሚና ለማጎልበት እንሰራለን – የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር

AMN – ሚያዝያ 07/2017

ስፖርት ለዘላቂ ሰላም ግንባታ ያለውን ሚና ለማጎልበት እንደሚሰራ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

ዓለም አቀፉ ‘ስፖርት ለልማትና ለሰላም ቀን’ በኢትዮጵያ ለ5ኛ ጊዜ በኦሮሚያ ክልል ቄለም ወለጋ ዞን ደምቢዶሎ ከተማ በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ይገኛል፡፡

በመርሐ-ግብሩ ላይ ስፖርት ለዘላቂ ሰላም፣ ለልማት እና ለአብሮነት ያለውን እምቅ አቅም ይበልጥ ለማጎልበት እንደሚሰራ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የስፖርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴዔታ መክዩ መሐመድ ተናግረዋል፡፡

ስፖርት እንደሀገር ወንድማማችነትን እና ገዢ ትርክትን ለማጠናከርም የማይተካ ሚና እንዳለው ሚኒስትር ዴዔታው አስታውቀዋል፡፡

ስፖርት ለልማትና ለሰላም ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ12ኛ ጊዜ እየተከበረ ይገኛል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review