ሸማቾች በግብይት ወቅት ማድረግ ያለባቸው ጥንቃቄዎች እና መውሰድ ያለባቸው እርምጃዎች ምንድናቸው ?

You are currently viewing ሸማቾች በግብይት ወቅት ማድረግ ያለባቸው ጥንቃቄዎች እና መውሰድ ያለባቸው እርምጃዎች ምንድናቸው ?

የንግድ ዕቃ ወይም አገልግሎት ከመግዛትዎ በፊት፣ በሚገዙበት ወቅት እና ከገዙ በኋላ ማድረግ የሚገባዎት ጥንቃቄ

ከመግዛትዎ በፊት

ስለሚገዙት እቃ ወይም አገልግሎት በቂና ትክክለኛ መረጃ ያላቸውን መሆኑን ማረጋገጥ፣

• በተጋነኑ ማስታወቂያዎች ተገፋፍቶ ለውሳኔ ያለመቸኮል፤

• ተጨማሪ መረጃዎችን ማሰባሰብ፣

• በማንኛውም ሁኔታ የሚገለጹ የዋጋ ቅናሽ ማስታወቂያዎችን ትክክለኛነት ማረጋገጥ፤

• በንግድ ቤቶች ስለ ዕቃዎች እና አገልግሎቶች የንግድ ዕቃ ወይም አገልግሎት የሚለጠፉ የዋጋ ዝርዝሮች ታክስ እና ሌሎች ሕጋዊ ክፍዎችን ያካተተ መሆኑን ማረጋገጥ፤

በሚገዙበት ወቅት

• ከክፍያ በፊት የገዙት የንግድ ዕቃ የዋስትና ወረቀት እና ውል ካለ የውሉን ኮፒ /የርስዎን ድርሻ/ መቀበልዎን፣

• በመጨረሻም ተገቢውን ክፍያ በመፈጸም ደረሰኞችን ወይም መግለጫዎችን ወይም ሌሎች ማስረጃዎችን መቀበልዎን አይዘንጉ፡፡

ከገዙ በኋላ

• ስለፈጸሙት ግዢ የሚያስረዱ ደረሰኞችን ወይም መግለጫዎችን ወይም ሌሎች ማስረጃዎችን በአግባቡ ማስቀመጥ፣

• የንግድ ዕቃው ወይም የአገልግሎት አጠቃቀም ማንዋል፣ የጥገናና ሌሎች የዋስትና ሰነዶችን በጥንቃቄ ማስቀመጥ፣

• የገዙት የንግድ ዕቃ ወይም አገልግሎት ጉድለት ያገኙበት እንደሆነ ግዢ ከፈጸሙበት ቀን ጀምሮ በ15 ቀን ጊዜ ውስጥ የንግድ ዕቃውን ወደገዙበት የንግድ ድርጅት ወይም ነጋዴ ጋር በመሄድ የንግድ ዕቃው አገልግሎት እንዲለወጥ ወይም ዋጋውን እንዲመለስ መጠየቅ፣

ምንጭ:-የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review