AMN – ጥር 5/2017 ዓ.ም
ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልእክት ዛሬ ለመጀመሪያ ጊዜ ለጉብኝት ወደ ሀገራችን የመጡትን የዴንማርኳ ልዕልት ቤኔዲክቴን በጽሕፈት ቤታችን ተቀብያለሁ ብለዋል።

እየሰራን ባለነው በሕጻናት ድጋፍ እና ጥራት ያለው ትምህርት ለሁሉም ተደራሽ በማድረግ ዙሪያ በጋራ የምንሰራበት ግንኙነት መፍጠር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ፍሬያማ ውይይት አድርገናል ሲሉም ገልጸዋል።