”ቁርዓን – የእውቀትና የሰላም ምንጭ” በሚል መሪ ሐሳብ ሲካሄድ የቆየው ሀገር አቀፉ የቁርዓን ሒፍዝ ውድድር ተጠናቀቀ

You are currently viewing ”ቁርዓን – የእውቀትና የሰላም ምንጭ” በሚል መሪ ሐሳብ ሲካሄድ የቆየው ሀገር አቀፉ የቁርዓን ሒፍዝ ውድድር ተጠናቀቀ

AMN-መጋቢት 7/2017 ዓ.ም

”ቁርዓን – የእውቀትና የሰላም ምንጭ” በሚል መሪ ሐሳብ በሁለቱም ጾታዎች ሲካሄድ የቆየው ሀገር አቀፉ የቁርዓን ሒፍዝ ውድድር ተጠናቋል።

በዚሁ መሠረት በወንዶች ከኦሮሚያ ክልል ቃሪዕ ሳላሀዲን አብዱረህማን እንዲሁም በሴቶች ከአማራ ክልል ቃሪዕ ሀፍሷ ከድር የውድድሩ አሸናፊ ሆነዋል፡፡

ይህን ተከትሎም ሁለቱ አሸናፊዎች እያንዳንዳቸው የመኪና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡

በዚሁ ውድድር በወንዶች ከአማራ ክልል ቃሪዕ ሙሀመድ አወል ሁለተኛ እንዲሁም ከሶማሌ ክልል ቃሪዕ አብዱሏሂ ዑስማን ሦስተኛ ሲወጡ፤ በሴቶች ደግሞ ከኦሮሚያ ክልል ቃሪዕ ሱንዱስ አብዱረዛቅ ሁለተኛ እና ከሶማሌ ክልል ቃሪዕ አልያ ሙሀመድኑር ሦስተኛ ደረጃን ይዘዋል፡፡

ለቀሪዎቹ ተወዳዳሪዎችም እንደየደረጃቸው የገንዘብ እና የሐጅ ጉዞ ሽልማት መዘጋጀቱ ተመላክቷል፡፡

በአንዋር አህመድ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review