ቋሚ ኮሚቴው ለማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት የቅርብ ክትትልና ድጋፍ በመስጠት ከፍተኛ አቅም አየፈጠረ ነው ፡- የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ተፈራ ሞላ

AMN ህዳር 20/2017 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ ም/ቤት የመሠረተ ልማትና ማዘጋጃ ቤታዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ለማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት የቅርብ ክትትልና ድጋፍ በመስጠት ከፍተኛ አቅም አየፈጠረ መሆኑን ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ተፈራ ሞላ አስታወቁ

የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ግልጽነት ላይ ያተኮረ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ እየካሄደ ነው።

ጽ/ቤቱ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኩን ለመሠረተ ልማትና ማዘጋጃ ቤታዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት ነው ያዘጋጀው ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ም/ቤት የመሠረተ ልማትና ማዘጋጃ ቤታዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ግዛቸው አይካ ( ዶ/ር) አገልግሎቶቹን በተመለከተ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ መዘጋጀቱ ቋሚ ኮሚቴው ስራውንና የተቋማቱን ተልዕኮ በሚገባ ተረድቶ የጋራ ግብ ለማሳካት እንዲችል ያደርገዋል ብለዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ተፈራ ሞላ በበኩላቸው ቋሚ ኮሚቴው ለማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት የቅርብ ክትትልና ድጋፍ በመስጠት ከፍተኛ አቅም አየፈጠረ እንደሆነ ጠቅሰዋል።

የከተማ መሪ ጠንካራ ተቋም መገንባት እንደሚኖርበትም ጠቁመው በተቋም አደረጃጀትም የተለወጠ የሰው ኃይልን ግብአትና ቴክኖሎጂን አቀናጅቶ መምራት ይኖርበታል ነው ያሉት።

ጠንካራ ተቋም ሲገነባ ለማንም የማትበገር ጠንካራ ሀገር ትኖረናለችም ብለዋል።

በምትኩ ተሾመ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review