AMN- ጥቅምት 11/2017 ዓ.ም
በሀሰተኛ መታወቂያ ፣ የጋብቻ ሰርተፊኬት እና የልጃቸውን የልደት ሰርተፊኬት ለማግኘት የሞከሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አዲስ አበባ የሲቪል ምዝገባ እና የመኖሪያ አገልግሎት ኤጀንሲ አስታወቀ ፡፡
በየካ ወረዳ 7 የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ፅ/ቤት በቀን 29/1/2017 ዓ.ም በሀሰተኛ መታወቂያ የጋብቻ ሰርትፍኬት እና የልጃቸው ልደት ለማግኘት የሞከሩ ግለሰቦች በህግ ቁጥጥር ስር እንዲውሉ ተደርጎ ምርመራ እየተደረገባቸው እንደሚገኝ ነው ኤጀንሲው በመረጃው ያስታወቀው፡፡