በሁሉም የሀገሪቱ ማደያዎች የነዳጅ ግብይት በዲጂታል ሲስተም የክፍያ አማራጮች ብቻ እንዲፈፀም እየተሰራ ነው – የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር

You are currently viewing በሁሉም የሀገሪቱ ማደያዎች የነዳጅ ግብይት በዲጂታል ሲስተም የክፍያ አማራጮች ብቻ እንዲፈፀም እየተሰራ ነው – የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር

AMN- መስከረም 27/2017 ዓ.ም

በ2017 በጀት ዓመት በኢትዮጵያ በሚገኙ ሁሉም ማደያዎች የነዳጅ ግብይት በዲጂታል ሲስተም የክፍያ አማራጮች ብቻ እንዲፈፀም ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ።

የሚኒስቴሩ የነዳጅ የሪፎርም ስትሪንግ ኮሚቴ በ2017 በጀት ዓመት መሪ እቅድ እና በ2016 በጀት ዓመት የነዳጅ ሪፎርም እቅድ አፈፃፀም ላይ ተወያይቷል፡፡

ለስትሪንግ ኮሚቴው የ2017 በጀት ዓመት የነዳጅ ሪፎርም ማስተባበሪያ መሪ እቅድ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።

በበጀት ዓመቱ በሁሉም የሀገሪቱ ማደያዎች የነዳጅ ግብይት በዲጂታል ሲስተም የክፍያ አማራጮች ብቻ እንዲፈፀም በማድረግ በኩል በትኩረት እንደሚሰራ ተገልጿል።

የነዳጅ ሪፎርሙን የበለጠ ውጤታማ ለማድረግ ከነዳጅ አቅርቦት፣ ስርጭትና ተደራሽነት አንጻር እየተስተዋሉ ያሉ ክፍተቶችን ለማረም የአሰራር ስርዓት መዘርጋት እንደሚያስፈልግም ተመላክቷል፡፡

የ2016 በጀት ዓመት የነዳጅ ሪፎርም የአፈፃፀም ሪፖርት ቀርቦ በኮሚቴው መገምገሙን ከንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review