በህብረ ብሔራዊነት ማሳያዋ አዲስ አበባ የብሔሮች’ ብሔረሰቦች እና ህዝቦች በአል አብሮነትን እንዲሁም ህብረትን ባንፀባረቀ መልኩ ተከብሮ አልፏል ፡-አፈ ጉባኤ ቡዜና አልከድር

AMN – ታኅሣሥ 13/2017 ዓ.ም

በህብረ ብሔራዊነት ማሳያዋ አዲስ አበባ የብሔሮች’ ብሔረሰቦች እና ህዝቦች በአል አብሮነትን እንዲሁም ህብረትን ባንፀባረቀ መልኩ ተከብሮ አልፏል ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ቡዜና አልከድር ገለጹ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ለብሔሮች ‘ብሔረሰቦች እና ህዝቦች በአል በስኬታማ መልኩ መከበር ጉልህ አስተዋፅኦ ለተወጡ ተቋማቶች የምስጋና እና እዉቅና መርሀ ግብር እያከናወነ ነው፡፡

በሁሉም ኢትዮጽያዊያን የጋራ ቤት አዲስ አበባ የብሔሮች’ ብሔረሰቦችና ህዝቦች በአል በተለያዩ መርሀ ግብሮች በድምቀት ተከብሮ አልፏል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ቡዜና አልከድር በህብረ ብሔራዊነት ማሳያዋ አዲስ አበባ የብሔሮች’ ብሔረሰቦች እና ህዝቦች በዐል አብሮነትን እንዲሁም ህብረትን ባንፀባረቀ መልኩ ተከብሮ አልፏል ብለዋል፡፡

አዲስ አበባ በአሉን በህብረት እና በድምቀት በማክበር ልዩነትን እንደ ድምቀት የምትጠቀም እና አብሮነትን የምታጎላ ህብረ ብሔራዊ ከተማ መሆኗን ለዓለም አሳይታለች ብለዋል፡፡

የበአሉ ስኬታማ ሆኖ ማለፍ የተቋማት ቅንጅት እና መናበብ የሚደነቅ ስለመሆኑ የተናገሩት ዋና አፈ ጉባኤዋ ለዚህም ምስጋናን ችረናቸዋል ብለዋል፡፡

በተመስገን ይመር

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review