AMN – ጥር 6/2017 ዓ.ም
በ2017 በጀት ዓመት በስድስት ወራት ውስጥ በነዳጅ ምርት ስርጭት ላይ በህገ ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ በነበሩ ላይ ህጋዊ እርምጃ መውሰዱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ አስታወቀ
ቢሮው ባለፉት ስድስት ወራት በነዳጅ ምርት ስርጭት፣ቁጥጥር እና በተወሰዱ ርምጃዎች ላይ መግለጫ ሰጥቷል።
የቢሮው ኃላፊ አቶ ሐቢባ ሲራጅ በሰጡት መግለጫ እንደ ሀገር የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን መነሻ በማድረግ እገ ወጥነት እንዳይሰፍን በልዩ ትኩረት ሲሰራ መቆየቱን ተናግረዋል።
በዚህም የነዳጅ አቅርቦቱንና ቁጥጥሩን በማጠናከር ሊከሰቱ የሚችሉ ህገወጥ ተግባራትን መከላከል ስለመቻሉ አንስተዋል።
በግማሽ በጀት ዓመቱ በከተማው በ125 ማደያዎች በአማካኝ ናፍጣ በቀን 2.0 ሚሊዮን ሊትር ፣ ቤንዚን 1.45 ሚሊዮን ሊትር በድምሩ 3.45 ሚሊየን ሊትር ነዳጅ ማቅረብ ስለመቻሉ ተናግረዋል ።
የነዳጅ ግብይቱን ተአማኒነት ለማረጋገጥም የሁሉንም የነዳጅ ማደያዎች የዕለታዊ የምርት ስርጭት አቅርቦትን ለህዝብ ይፋ ስለመደረጉም ኃላፊው ተናግረዋል።
በተሰሩ የቁጥጥር እና የክትትል ስራዎችም በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ ቤንዚን 18 ሺህ 985 ሊትር ፣ ናፍጣ 9 ሺህ 434.5 እና ነጭ ጋዝ 189 በድምሩ 28 ሺህ 608.5 ሊትር ነዳጅ ተገኝቶ እንዲወረስ መደረጉንም የቢሮ ሀላፊው አመልክተዋል።
በነዳጅ ግብይት ላይ በህገወጥ መልኩ የሚገበያዩትን ጭምር ተጠያቂ ከማድረግ ጀምሮ በርካታ ስራዎች መከናወናቸውን አንስተዋል፡፡
በዚህም ማደያዎች ለ24 ሰዓት እንዲሰሩ በማድረግ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችም መከናወናቸውን ጠቁመዋል።
በራሄል አበበ
All reactions:
3030