በሊባኖስ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 125 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

You are currently viewing በሊባኖስ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 125 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

AMN- ጥቅምት 18/2017 ዓ.ም

በሊባኖስ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 125 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በሊባኖስ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገራቸው ለመመለስ ከባለድርሻ አካላት ጋር በልዩ ትኩረት እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ገልጿል።

ከሊባኖስ እንዲመለሱ የተደረገውም በዚህ ጥረት መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቤይሩት ከሚገኘው የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ቆንስላ ጄኔራል ጽሕፈት ቤት ጋር በመሆን በቀጣይም ሌሎች ለችግር ተጋላጭ የሆኑ ዜጎችን ወደ ሀገራቸው ለመመለስ አስፈላጊውን ጥረት እያደረገ እንደሚገኝም አስታውቋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review