AMN-መስከረም 28/2017 ዓ.ም
በሊባኖስ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 51 ኢትዮጵያውያን ወደ አገራቸው ተመልሰዋል።
በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱም ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ፣ሴቶች እና ማኀበራዊ ጉዳዮች ሚኒስቴር እና ከኢትዮጵያ አደጋ ሥጋት አመራር ኮሚሽን ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብያት ጌታቸው ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት ከዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ ሥራዎች ቀዳሚ ትኩረቱን በሊባኖስ ለሚገኙ ኢትዮጵያውያን በማድረግ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
ከሊባኖስ ዛሬ የተመለሱት ዜጎቻችንም አንዱ የተግባር የእንቅስቃሴው መገለጫ ነው ብለዋል።
በቀጣይም ሌሎች ለችግር ተጋላጭ የሆኑ ዜጎቻችንን ወደ አገራቸው ለመመለስ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር እየተሠራ መሆኑን መናገራቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል።