በሊባኖስ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ለመመለስ እንዲመዘገቡ በድጋሚ ጥሪ ቀረበ

You are currently viewing በሊባኖስ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ለመመለስ እንዲመዘገቡ በድጋሚ ጥሪ ቀረበ

AMN-መስከረም 22/2017 ዓ.ም

በሊባኖስ የሚኖሩ ወደ ሀገራቸው መመለስ የሚፈልጉ ኢትዮጵያውያን እንዲመዘገቡ በቤሩት የሚገኘው የኢትዮጵያ ቆንስላ ጀነራል ጽ/ቤት ጥሪ አቅርቧል፡፡

በሊባኖስ በተከሰተው ጦርነት ምክንያት ወደ ሀገራቸው መመለስ የሚፈልጉ ኢትዮጵያውያን ከሊባኖስ መውጣት የሚችሉበትን መንገድ እያመቻቸ መሆኑን ቆንስላ ጽሕፈት ቤቱ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡

በመሆኑም ወደ ሀገራቸው መመለስ የሚፈልጉ እና እስከ አሁን ያልተመዘገቡ ዜጎች አስፈላጊውን መረጃ በማዘጋጀት እንዲመዘገቡ ሲልም ነው ጥሪ ያቀረበው፡፡

በዚህም መሠረት፤ ሙሉ ስም ከነአያት (ፓስፓርት ላይ እንደተፃፈው)፣ የፓስፖርት ቁጥር፣ በሊባኖስ የቆይታ ጊዜ እና የሊባኖስ ስልክ ቁጥሮች ለምዝገባ አስፈላጊዎቹ መረጃዎች መሆናቸውን ጽሕፈት ቤቱ ገልጿል፡፡

ለምዝገባ የተዘጋጁት ስልክ ቁጥሮችም÷ 03-29-89-78፣ 76-03-08-23፣ 81-99-46-34፣ 70-29-80-91፣ 81-80-25-18፣ 70-84-25-24 እና 81-09-27-46 መሆናቸውን ጽ/ቤቱ በመረጃው አስታውቋል፡፡

ቀደም ሲል በቀረበው ጥሪ መሰረትም የተመዘገቡ ዜጎች በድጋሚ መመዝገብ እንደማያስፈልጋቸው ጽ/ቤቱ አስታውቋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review