በልምድ እና በውርስ የተገኙ እውቀቶችን መጠበቅና እውቅና መስጠት ለኢኮኖሚ ዕድገት ትልቅ አስተዋጽዖ ያበረክታል- ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል

You are currently viewing በልምድ እና በውርስ የተገኙ እውቀቶችን መጠበቅና እውቅና መስጠት ለኢኮኖሚ ዕድገት ትልቅ አስተዋጽዖ ያበረክታል- ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል

AMN-መስከረም 20/2017 ዓ.ም

በልምድ እና በውርስ የተገኙ እውቀቶችን በመጠበቅ፣ በመንከባከብ እና እውቅና በመስጠት ለሀገሪቱ ኢኮኖሚ ትልቅ አስተዋጽዖ ማበርከት እንደሚቻል የስራና ክህሎት ሚኒስትሯ ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ተናገሩ ::

የስራና ክህሎት ሚኒስቴር በልምድ የተገኘ ብቃት እውቅና አሰጣጥ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር እያካሄደ ይገኛል::

በኢትዮጵያ ያልተመሰከረላቸው እና ያልተደረሰባቸው በርካታ ባለሙያዎች መኖራቸውን የገለጹት የስራና ክህሎት ሚኒስትሯ ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል፣ በልምድ እና በውርስ የተገኙ እውቀቶችን በመጠበቅ፣ በመንከባከብ እና እውቅና በመስጠት ለሀገሪቱ ኢኮኖሚ ትልቅ አስተዋጽዖ ማበርከት እንደሚቻል ተናግረዋል::

ዜጎችንና ሀገርን የሚያስከብሩ በርካታ ሙያዎች በኢትዮጵያ እንዳሉ የገለፁት ሚኒስትሯ ዜጎች ላላቸው እውቀት እና ለሰሩት ስራ እውቅና መስጠት የዜጎችን የራስ መተማመን ለማሳደግ ብሎም አካታችነትን እና ፍትሃዊነትን ለማረጋገጥ ያስችላል ብለዋል፡፡

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ኢትዮጵያዊያንን ቢያንስ የአንድ ሙያ ባለቤት ለማድረግ እየሰራ እንደሚገኝ ተመላክቷል::

በሚቀጥሉት አመታትም እውቅና የመስጠት ተግባሩ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተመላክቷል፡፡

በቴዎድሮስ ይሳ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review