AMN – የካቲት 18/2017 ዓ.ም
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ዛሬ ባካሄደው የልዩ የውጭ ምንዛሬ ጨረታው ላይ 27 ባንኮች መሳተፋቸውን ገልጿል።
ባንኮቹ በአማካይ አንድ የአሜሪካን ዶላር ለመግዛት 135 ነጥብ 6185 ብር ማቅረባቸውም ተመላክቷል፡፡
ብሔራዊ ባንክ በልዩ የውጭ ምንዛሬ ጨረታው ላይ በርካታ ባንኮች መሳተፋቸው መልካም የሚባል መሆኑን ገልጿል።
በቀጣይም የውጭ ምንዛሪ ገበያ ሁኔታን በቅርበት በመከታተል እንደ አስፈላጊነቱ ተጨማሪ የውጭ ምንዛሪ ሽያጮችን እንደሚያካሂድ መጠቆሙን ከኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ የትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡