በሎስ አንጀለስ የተከሰተው የሰደድ እሳት በቁጥጥር ሥር መዋሉ ተገለጸ

You are currently viewing በሎስ አንጀለስ የተከሰተው የሰደድ እሳት በቁጥጥር ሥር መዋሉ ተገለጸ
Water is dropped on a large brush fire in the early morning hours Friday in Sylmar, Calif. At least 25 structures have been destroyed.
  • Post category:ዓለም

AMN – ጥር 2/2017 ዓ.ም

የሀገሪቱ ባለሥልጣናት በሎስ አንጀለስ የተከሰተውን የሰደድ እሳት በቁጥጥር ሥር ማዋል በመቻሉ ነዋሪዎች አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ የተላለፈው ትዕዛዝ መሻሩን አስታውቀዋል፡፡

የሎስ አንጀለስ እሳት መከላከል ዲፓርትመንት ነዋሪዎች ወደ ቀዬአቸው በሚመለሱበት ወቅት ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው አሳስቧል፡፡

በሎስ አንጀለስና አካባቢው ከሰሞኑ ከ80 ስኩዌር ኪሎ ሜትር በላይ የሚሸፍን የሰደድ እሳት ተከስቷል፡፡

በአደጋውም እስከ አሁን ድረስ የ10 ሠዎች ህይወት ማለፉ የተገለጸ ሲሆን 2ሺ የመኖሪያ እና ንግድ ቤቶች ወድመዋል፡፡

100ሺ ነዋሪዎችም ከአካባቢው ለመሸሽ ተገደዋል፡፡

ይህን ተከትሎ ተመራጩ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ዲሞክራት መራሿ ግዛት ከድንገተኛ የሰደድ እሳት መከላከል ጋር ተያይዞ ያላትን ደካማ ፖሊሲ ያሳያል ሲሉ በትዊተር ገጻቸው ላይ ትችት ሰንዝረዋል፡፡

የካሊፎርኒያው አስተዳዳሪ ጋቪን ኒውሶምም ሥልጣናቸውን ሊለቁ እንደሚገባ አክለዋል ትራምፕ፡፡

ሌሎችም በተመሳሳይ መልኩ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ለቀውሱ የሰጡት ትኩረት አናሳ መሆኑን በማንሳት በአብነትም በዚህ አስቸጋሪ ጊዜ ላይ ሆነው ለዩክሬን የ500 ሚሊዮን ዶላር ወታደራዊ ድጋፍ ማድረጋቸው አንስተዋል፡፡

የበሎስ አንጀለሱ ከንቲባ ካሬን ባዝ ከ17 ሚሊዮን ዶላር በላይ የከተማዋን የድንገተኛ እሳት መከላከያ ዲፓርትመንት በጀት መቀነሳቸው እና አደጋው እንደሚከሰት እየተገለጸ ባለበት ወቅት ወደ አፍሪካ ጉዞ ማድረጋቸው እያስወቀሳቸው ከመሆኑም በላይ ሥልጣን እዲለቁ ጥሪ እየቀረበላቸው ይገኛል፡፡

ማክሰኞ እለት የተቀሰቀሰው እና ፓሊሳድስ የሚል ስያሜ የተሰጠው የሰደድ እሳት 5 ጊዜ ተከስቶ በርካታ ጉዳት ያደረሰ ሲሆን የዝነኛ ሰዎችን መኖሪያ ቤት፣ ባንኮችን፣ ካፍቴሪያዎች እና ሌሎችንም አውድሟል፡

እሳቱ በንፋስ ኃይል ታግዞ ተጨማሪ ጉዳት እንዳያደርስ ሥጋት መኖሩን ከቢቢሲ እና አርቲ የተገኙ መረጃዎች ያመለክታል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review