በሕዝቦች መካከል አንድነት፣ መቀራረብ፣ ወንድማማችነት፣ እህትማማችንት ታሪካዊ እና ትርክታዊ ትስስር እየጠነከረ መጥቶ ኢትዮጵያ አንገቷን ቀና እያረገች ትገኛለች ሲሉ የብልፅግና ፓርቲ የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ ሚኒስትር ቢቂላ ሁሪሳ(ዶ.ር) ገለጹ፡፡
“የድህረ እውነት ዘመን በእውነት እና በእውቀት” በሚል መሪ ሀሳብ ለሲዳማ ክልል አመራሮች እና የሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን ባለሙያዎች የተዘጋጀው ስልጠና መካሄድ ጀምሯል፡፡
በስልጠና መድረኩ የብልፅግና ፓርቲ የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ ሚኒስትር ቢቂላ ሁሪሳ(ዶ.ር)፣ በሕዝቦች መካከል አንድነት፣ መቀራረብ፣ ወንድማማችነት/ እህትማማችንት ታሪካዊና ትርክታዊ ትስስር እየጠነከረ መጥቶ ኢትዮጵያ አንገቷን ቀና እያረገች ትገኛለች ብለዋል፡፡
በድሀረ እውነት ዘመን አፍራሽ ሃይሎች ሆን ተብሎ ስሜት ቀስቃሽ ንግግሮች በመጠቀም ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው አንድነትና ወንድማማችነት/ እህትማማችነት እሴት ለማፍረስ እየሰሩ በመሆኑ በእውነትና በእውቀት መመከት ይገባል ብለዋል፡፡
አመራሩና ባለሙያው የድህረ እውነት ዘመንን ተረድቶ እውነትንና እውቀትን በመጨበጥ ሆን ተብለው ሕዝብን ከሕዝብ ለማጋጨትና ሀገር ለማፍረስ በውስጥና በውጭ የሚቀነባበሩ የሀሰት መረጃዎችን መመከት አስፈላጊ ነው ማለታቸውን ከፓርቲው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡