በሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ወንጀል ጥፋተኛ የተባሉ ግለሰቦች እስከ 25 ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራት ተቀጡ

You are currently viewing በሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ወንጀል ጥፋተኛ የተባሉ ግለሰቦች እስከ 25 ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራት ተቀጡ

AMN – ጥቅምት 7/2017 ዓ.ም

በሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ወንጀል ጥፋተኛ ተብለው በ13 መዝገብ የተከሰሱ ግለሰቦች ከአንድ ዓመት እስከ 25 ዓመት ፅኑ እስራት መቀጣታቸውን ፌዴራል ፖሊስ አስታውቋል፡፡

በ13 የክስ መዝገብ ተከሰው የፍርድ ውሳኔ የተላለፈባቸው፡-

1ኛ. ተካ ወ/ማርያም 25 ዓመት ጽኑ እስራት እና 28 ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት፤ በሌላ የክስ

መዝገብ ደግሞ 16 ዓመት ከ6 ወር ጽኑ እስራት፣

2ኛ. ለማ ተማሮ 10 ዓመት ጽኑ እስራት፣

3ኛ. መለሰ ካህሳይ 11 ዓመት ጽኑ እስራትና 76 ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት፣

4ኛ. ደመቀች ማጉጂ 15 ዓመት እስራት እና 30 ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት፣

5ኛ. ስምኦን ተወልደ 3 ዓመት ከ7 ወር እስራት እና 4 ሺህ 500 ብር የገንዘብ ቅጣት ፣

6ኛ. ዮሃንስ ፍስሃዩ 5 ዓመት ከ7 ወር እስራትና 7 ሺህ 500 ብር የገንዘብ ቅጣት፣

7ኛ. ሀና ዲኖ 3 ዓመት ከ3 ወር እስራትና 2 ሺህ 500 ብር የገንዘብ ቅጣት፣

8ኛ. ረዳት ሳጅን መሀመድ አህመድ 6 ዓመት እና 8 ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት፣

9ኛ. ገ/ትንሳኤ ሀጎስ በ16 ዓመት ከ6 ወር ጽኑ እስራት እና 80 ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት፣

10ኛ. አብዱል ሽኩር ይማም 10 ዓመት እና 11 ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት፣

11ኛ. ሙህዲን አማን መሀመድ 10 ዓመት እና 11 ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት፣

12ኛ. አብዱላዚዝ ራህመቶ ዳንቴቦ 5 ዓመት እና 6 ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት፣

13ኛ. ዘላለም ብርሃኑ 5 ዓመት እስራት እና 3 ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት፣

14ኛ. ናርዶስ ሀብቴ ደበሌ 4 ዓመት ከ5 ወር እስራት እና 3 ሺህ 500 ብር የገንበዘብ ቅጣት፣

15ኛ. ፍሬሕይወት በላይ ግርማ 6 ዓመት እስራት እና 110 ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት፣

16ኛ. ቅዱስ ኃ/ሚካኤል ሳምቢ 4 ዓመት ከ5 ወር እስራት እና 3500 ብር የገንዘብ ቅጣት፣

17ኛ. ሚኪያስ ተሾመ ፈጡላ 410 ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት በ13 የምርመራ መዝገቦች ሲታይ የቆየውን የሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር የወንጀል መዝገብ መርምሮ ጥፋተኞችን ያርማል ሌሎችንም ያስተምራል በሚል ከአንድ ዓመት እስከ 25 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲሁም ከ2 ሺህ ብር እስከ 410 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ መወሰኑን ከፌዴራል ፖሊስ የተገኘ መረጃ ያሳያል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review